LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5
JT-SlideShow-Footer

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የጣና ሀይቅና ሌሎች ዉሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ (ጣዉጥልኤ)

Amhara National Regional State

Lake Tana and Other Water bodies Protection and Development Agency (LTaOWPDA)

የጣና ሀይቅና ሌሎች ዉሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በአማራ ክልል /ቤት ደንብ ቁጥር 180/11 የተቋቋመ /ቤት ነዉ፡፡ ለኤጀንሲዉ አቅጣጫ የሚሰጥና ድጋፍ የሚያደርግ በክልሉ /ርዕሰ መስተዳደር የሚመራ የጣና ሀይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ምክር ቤት አለዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኤጀንሲዉ ደንብ ቁጥር 158/10 የተቋቋመና በክልሉ /መስተዳደር የሚሰየም ሰብሳቢ ያለዉ ቦርድ የሚመራ የጣና ሐይቅና አካባቢው ደህንነት ፈንድ አለዉ፡፡

ዓላማዉ የጣና ሀይቅና አካባቢዉን ጨምሮ በአማራ ክልል የሚገኙትን ሌሎች ዉሃአካላትና ዉሃአዘል መሬቶችን እና የወንዞችን ስርዓተ-ምህዳር እዉቀትን መሠረት በማድረግ በዘላቂነት በመንከባከብ ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነዉ፡፡

ተግባርና ሀላፊነት

ኤጀንሲዉ በጣና ሀይቅና አካባቢዉ፤በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ሀይቆች እንዲሁም ወንዞችና የዉሃአዘል መሬት ሥርዓተ-ምህዳሮች እየደረሰ ያለዉን፡

የተስፋፊ መጤ ዝርያ መከሰትና መስፋፋት በተለይ በጣና ሀይቅ ላይ በመስፋፋት ከፍተኛ ሥነ-ምህዳራዊና ሶሾ-ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ እያስከተለ ያለዉን የእንቦጭ መጤ አረም

የሥርዓተ ምህዳሮቹ ብዝሃ ህይዎት መመናመንና የመጥፋት ሥጋት

ከከተሞች፤ኢንዱስትሪዎችና የግብርና ተግባራት በቀጥታ በሚለቀቁ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ እየደረሰ ያለዉ የዉሃ ብክለት

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች በማባባስ ከፍተኛ ሚና ያለዉ የተፋሰስ መራቆት በተለይ በወንዞችና በሀይቆች ዳርቻ የአረንጓዴ ድንበር (Buffer zone) የጣና ሀይቅ ዳርቻ አለመከለልና ተግባራዊ አለመሆን በዚህም ከሥርዓተ-ምህዳሮቹ ልናገኛቸዉ የሚገቡ ሥነ-ምህዳራዊ እና የአካባቢዉን ህብረተሰብ ኑሮ የሚያሻሽሉ ሶሾ-ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እየቀነሱ በመምጣታቸዉና ተግዳሮቶቹን በፍጥነትና በዘላቂነት ለመቅረፍ፤ (1) በዉሃ ሀብት አጠቃቀምና በተፋሰስ ልማት፤ በዉሃ ብክለት ቁጥጥር ከሚሰሩ የፌደራልና ክልል አጋር አካላት ጋር በጋራ ማቀድ፤መተግበርና መገምገም (2) ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማከናወን (3) የጥናት ዉጤቶችንና ሌሎች ተሞክሮዎችን/የቴክኖሎጂ ማላመድን ጭምር/ በመቀመር የስልጠና ማንዋልና የአሰራር መመሪያዎችን ከሚመለከታቸዉ ጋር በመተባበር ማዘጋጀት (4) በቅንጅት የሚሰሩትንም ሆነ በኤጀንሲዉ የሚከናወኑትን ተግባራት በየጊዜዉ መቆጣጠር፤መደገፍና መገምገም (5) እያደገ የመጣዉን የዜጎች በአካባቢ ያገባኛል ጉዳይ ላይ/ በተለይ በጣና ሀይቅ/ በአግባቡ ለማስተናገድ የበጎ አድራጎት ፍላጎት ሥርዓት መዘርጋት (6) የዓለምዓቀፍ ማህበረሰብም በተለይ የጣና ሀይቅ አካባቢ የዩኔስኮ ባዮስፌር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በምርምርና በልማት ትከረቶች ከፍተኛ በመሆናቸዉ በዚሁ ልክ ያደገ የአጋርነት ሥርዓት መፍጠር የአጀንሲዉ ቁልፍ ተግባራት ናቸዉ፡፡

በአጠቃላይ በጣና ሀይቅ ላይ በመስፋፋት ከፍተኛ ሥነ-ምህዳራዊና ሶሾ-ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ እያስከተለ ያለዉን የእንቦጭ መጤ አረም በአጭር ጊዜ ጉዳት በማያደርስ ደረጃ ለመቀነስ፤ በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ዉሃ አካላት (ሀይቆች፤ወንዞችና ዉሃአዘል መሬቶች) ሥርዓተ-ምህዳር በከፍተኛ ፍጥነት እየደረሰባቸዉ ያለዉን ችግር በመለየትና በፍጥነት ወደ መፍትሄዉ ለመሄድ 2012 ኤጀንሲዉ በርካታ እቅዶችን አስቀምጧል፡፡

Lake Tana and Other Water bodies Protection and Development Agency (LTaOWPDA) is responsible to conduct Research, prepare management and implementation plan, provide knowledge based support and advices, use appropriate emerging technologies, conduct training and prepare guideline manuals, Monitoring and Evaluation, policy revision, and create national and international partnerships

ON

Invasive Alien Species, Biodiversity Conservation, Water pollution and Waste Management, Integrated Water and Watershed Management, and Create job Opportunities

IN

Lake Tana Environment and Other regional Water bodies (lakes, Rivers, Streams, reservoirs, Wetlands, Dams) associated buffer zones

 

We have 2 guests online
Members : 6
Content : 72
Web Links : 2
Content View Hits : 5286
Vote Our Service
 

| |